课程进行中

እከክ፡ በፌደራል እና በወረዳ ደረጃ የጤና ባለሙያዎች የቆዳ ላይ ትኩረትን የሚሹ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች ስልጠና

提供者 OpenWHO
እከክ፡ በፌደራል እና በወረዳ ደረጃ የጤና ባለሙያዎች የቆዳ ላይ ትኩረትን የሚሹ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች ስልጠና

እከክ በመላው ዓለም ይገኛል። በመላው ዓለም በአንድ ጊዜ ከ200 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በበሽታው ይጠቃሉ። በሽታው በአብዛኛው የግብዓት ውስንነት (resource-poor) ባላቸው ሃሩራማ ሀገራት ላይ ኢንደሚክ (endemic) ነው፣ በአማካይም ከ5 – 10% ያህል ህጻናትን ያጠቃል። በተለይም ህዝብ ተጨናንቆ በሚኖርባቸውና ድህነት በአንድ ላይ በሚገኙባቸው ማህበረሰቦች የተለመደ ነው፣ እንዲሁም ህክምና ተደራሽ ባልሆነባቸው ቦታዎች። ይህ ኮርስ የበሽታውን ስርጭት፣ የበሽታውን ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ህክምና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እና የህብረተሰብ ጤና ቁጥጥርን ይመለከታል።

ምንጭ : WHO/Aya Yajima

自学
语言: አማርኛ
Scabies

课程信息

ይህ ኮርስ በሚከተሉት ቋንቋዎችም ይገኛል።

English - Русский - français - Español - português - العربية - Bahasa Indonesia- català- 中文

የእከክ በሽታ በወረዳ ደረጃ በሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የበሽታውን መኖር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጠረጥሩ ወይም ሊያረጋግጡ ይችላሉ። በበሽታው ለተጠቁ ግለሰቦች እና ከነሱ ጋር የቅርብ ንክኪ ላላቸው ሰዎች ውጤታማ የሆነ ህክምና ሲኖር፣ ለማህበረሰብ ደግሞ ማህበረሰብ አቀፍ የመድሃኒት እደላ አለ። የዚህ ስልጠና ዓላማም ስለእከክ በሽታ መረጃ መስጠት እና በፌደራልና በወረዳ ደረጃ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን እውቀት እና ክህሎት ለመጨመር ነው።

የትምህርቱ ዓላማዎች:

የስልጠናው መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቁ:

  • የእከክ በሽታ ስርጭትን መረዳት፣
  • የበሽታውን ምልክቶችና አቀራረብ መግለጽ፣
  • ምርመራው እንዴት እንደሚከናወን መረዳት፣
  • እከክ እንዴት እንደሚታከም ማብራራት፣
  • ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች መረዳት፣ እና
  • የህብረተሰብ ጤና ጣልቃ-ገብነት።

የኮርሱ ቆይታ: በግምት አንድ ሰዓት.

የኮርሱ ቆይታ: በግምት አንድ ሰዓት ነው።:

የምስክር ወረቀትን በተመለከተ፡ በመጨረሻው ምዘና ቢያንስ 80% ላስመዘገቡ ተሳታፊዎች የውጤታማነት ሰርተፍኬት ይኖራል። የስኬት የምስክር ወረቀት የተቀበሉ ተሳታፊዎች የዚህ ኮርስ የሰልጠና መረጃዎችን በነፃ ማውረድ ይችላሉ። እንዴት እንደሆነ ለማወቅ እዚህ ይጫኑ

የተተረጎመዉ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ቋንቋ Scabies: Training of health workers at national and district levels on skin-NTDs, 2021 የአለም የጤና ደርጅት ለዚህ የትርጉም ስራ ይዘት ወይም ትክክለኛነት ኃላፊነት አይወስድም። በእንግሊዝኛዉ እና በአማረኛዉ ትርጉም መካከል ልዩነት ከተፈጠረ የመጀመሪያው የእንግሊዝኛ ስሪት አስገዳጅ እና ትክክለኛ ስሪት ይሆናል።

ይህ የትርጉም ስራ በአለም የጤና ደርጅት አልተረጋገጠም። ይህ ግባዓት ለትምህርት ድጋፍ ዓላማዎች ብቻ የታሰበ ነው።

课程内容

  • ሞዱል 1፡ መግቢያ:

    ይህ የመግቢያ ሞዱል ትኩረትን የሚሹ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች (NTDs) ፣ የቆዳ ላይ-NTDs እና የእከክ በሽታን አጠቃላይ ምልከታ ይሰጣል።
  • ይህ የመግቢያ ሞዱል ትኩረትን የሚሹ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች (NTDs) ፣ የቆዳ ላይ-NTDs እና የእከክ በሽታን አጠቃላይ ምልከታ ይሰጣል።:

    በዚህ ሞዱል መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቅ፡ የበሽታ አምጪ መንስኤው ምን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚተላለፍ ማብራራት ፣ የእከክ በሽታ ጋር ተዛማች የሆኑ አጋላጭ ሁኔታዎችን ማብራራት፣ የእከክ በሽታን ስነ ምድራዊ ስርጭት እና መጠን መግለጽ፣ የዕድሜ እና የጾታ ስርጭትን መረዳት።
  • ሞዱል 3፡ የበሽታው ባህሪዎች (Clinical features):

    በዚህ ሞዱል መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡ የእከክ በሽታን የልጆች እና የአዋቂዎች የሰውነት ላይ ስርጭት ማብራራት ፣ አይነተኛ በሆነው እና በcrusted scabies መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት፣ እና ከእከክ በሽታ ጋር ተያየዘው የሚመጡ ችግሮችን መግለጽ።
  • ሞዱል 4፡ ምርመራ እና ህክምና:

    በዚህ ሞዱል መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡የእከክ በሽታን ምርመራ ለማካሄድ የስምምነት መስፈርቶችን መጠቀም፣የእከክ በሽታን ለመመርመር የሚጠቅሙትን ማይክሮስኮፒና ደርሞስኮፒን መረዳት፣ ለመሳሰሉ የሚችሉ በሽታዎችን ለይቶ መዘርዘር፣ የሚገኙትን የሕክምና አማራጮች መረዳት፣ እና መድሀኒቶቹ መሰጠት የማይኖርባቸውና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ማብራራጥ
  • ሞዱል 5: የህብረተሰብ ጤና አኳያ ያለው እንድምታ:

    በዚህ ሞዱል መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡የእከክ በሽታን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዱሁም ሥነ ልቦናዊ ተፅእኖ ማብራራት ፣ በትንሹ መመዝገብ ያለባቸውን ተለዋዋጮች (variables) መዘርዘር፣ እና የእከክ በሽታ የህብረተሰብ ጤና ጣልቃ-ገብነቶችና ቁጥጥርን ማብራራጥ

订阅本课程

该课程是免费的。 只需在OpenWHO上注册一个帐户并参加课程!
现在注册吧

证书要求

  • 课程证书 授予者需要至少取得课程总分的百分之 80%
  • 完成课程可获得开放徽章