Course is available
እከክ በመላው ዓለም ይገኛል። በመላው ዓለም በአንድ ጊዜ ከ200 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በበሽታው ይጠቃሉ። በሽታው በአብዛኛው የግብዓት ውስንነት (resource-poor) ባላቸው ሃሩራማ ሀገራት ላይ ኢንደሚክ (endemic) ነው፣ በአማካይም ከ5 – 10% ያህል ህጻናትን ያጠቃል። በተለይም ህዝብ ተጨናንቆ በሚኖርባቸውና ድህነት በአንድ ላይ በሚገኙባቸው ማህበረሰቦች የተለመደ ነው፣ እንዲሁም ህክምና ተደራሽ ባልሆነባቸው ቦታዎች። ይህ ኮርስ የበሽታውን ስርጭት፣ የበሽታውን ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ህክምና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እና የህብረተሰብ ጤና ቁጥጥርን ይመለከታል።
ምንጭ : WHO/Aya Yajima
ይህ ኮርስ በሚከተሉት ቋንቋዎችም ይገኛል።
English - Русский - français - Español - português - العربية - Bahasa Indonesia
የእከክ በሽታ በወረዳ ደረጃ በሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የበሽታውን መኖር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጠረጥሩ ወይም ሊያረጋግጡ ይችላሉ። በበሽታው ለተጠቁ ግለሰቦች እና ከነሱ ጋር የቅርብ ንክኪ ላላቸው ሰዎች ውጤታማ የሆነ ህክምና ሲኖር፣ ለማህበረሰብ ደግሞ ማህበረሰብ አቀፍ የመድሃኒት እደላ አለ። የዚህ ስልጠና ዓላማም ስለእከክ በሽታ መረጃ መስጠት እና በፌደራልና በወረዳ ደረጃ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን እውቀት እና ክህሎት ለመጨመር ነው።
የትምህርቱ ዓላማዎች:
የስልጠናው መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቁ:
የኮርሱ ቆይታ: በግምት አንድ ሰዓት.
የኮርሱ ቆይታ: በግምት አንድ ሰዓት ነው።:
የምስክር ወረቀትን በተመለከተ፡ በመጨረሻው ምዘና ቢያንስ 80% ላስመዘገቡ ተሳታፊዎች የውጤታማነት ሰርተፍኬት ይኖራል። የስኬት የምስክር ወረቀት የተቀበሉ ተሳታፊዎች የዚህ ኮርስ የሰልጠና መረጃዎችን በነፃ ማውረድ ይችላሉ። እንዴት እንደሆነ ለማወቅ እዚህ ይጫኑ።
የተተረጎመዉ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ቋንቋ Scabies: Training of health workers at national and district levels on skin-NTDs, 2021 የአለም የጤና ደርጅት ለዚህ የትርጉም ስራ ይዘት ወይም ትክክለኛነት ኃላፊነት አይወስድም። በእንግሊዝኛዉ እና በአማረኛዉ ትርጉም መካከል ልዩነት ከተፈጠረ የመጀመሪያው የእንግሊዝኛ ስሪት አስገዳጅ እና ትክክለኛ ስሪት ይሆናል።
ይህ የትርጉም ስራ በአለም የጤና ደርጅት አልተረጋገጠም። ይህ ግባዓት ለትምህርት ድጋፍ ዓላማዎች ብቻ የታሰበ ነው።