Please log in to proceed.

Course is available

ተላላፊ ያልሆነው የዝሆኔ በሽታ ፖዶኮኒኦሲስ በፌደራል እና በወረዳ ደረጃ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና

Offered by OpenWHO
ተላላፊ ያልሆነው የዝሆኔ በሽታ ፖዶኮኒኦሲስ በፌደራል እና በወረዳ ደረጃ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና

በአጠቃላይ የቆዳ በሽታዎች በጣም የተለመዱ ናቸው, ይህም ማለት ከ 10 እስከ 30% የሚሆነውን የጤና ሰራተኛ እርዳታ ፈላጊ ታካሚዎችን መጠን ይይዛሉ. ስለዚህም፣ ቆዳ የተለያዩ የቆዳ ላይ ትኩረትን የሚሹ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች ለማወቅ ፍንጭ ከመስጠትም በላይ፣ በከፍተኛ የበሽታ ጫና እና ድህነት ውስጥ ባሉ ህዝቦች ላይ ሌሎች የተለመዱ በሽታዎች መኖራቸውን ማረጋገጫ እና ተመሳሳይ የሆኑ በሽታዎችን መለያ ነው።

የፎቶ ምንጭ: ከበደ ደርቤ

Self-paced
Language: አማርኛ
Podoconiosis

Course information

ይህ ኮርስ በሚቀጥሉት ቋንቋዎችም ይገኛል:

English

የስልጠናው አጠቃላይ ምልከታ: ተላላፊ ያልሆነው የዝሆኔ በሽታ(ፖዶኮኒኦሲስ) በተወሰኑ ሃገራት የተለመደ ስለሆነ እንደ በዝሆኔ በሽታ (ሊንፋቲክ፡፡ፊላሪያሲስ)፣ በፎከት (ኦንኮሰርካሲስ))፣ በስጋ ደዌ እና በህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አማካኝነት ከሚከሰተው የፍርንት እግር ላይ እብጠት መለየት አስፈላጊ ነው። የፖዶኮኒኦሲስ ህክምና በዓለም የጤና ድርጅት የዝሆኔ በሽታ (ሊንፋቲክ፡፡ፊላሪያሲስ) መከላከል እና ቁጥጥር ስር የሚካተትና የሚታከም ነው።

የዚህ ስልጠና ዓላማም ለጤና ባለሙያዎች ስለበሽታው ስርጭት፣ ምርመራ፣ ህክምና፣ ጫና እና ሪፖርት አደራረግ መሰረታዊ የሆነ እውቀት ማስጨበጥ ነው።

የትምህርቱ ዓላማዎች: የስልጠናው መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቁ:

  • በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፖዶኮኒኦሲስ በሽታ ስርጭትን መረዳት፣
  • የፖዶኮኒኦሲስ በሽታን ምልክቶችና አቀራረብ መግለጽ፣
  • ምርመራው እንዴት እንደሚከናወን መረዳት፣
  • የፍርንት የእግር ላይ እብጠት እንዴት እንደሚታከም ማብራራት፣
  • መረጃ እንዴት እንደሚጠናቀር እና ሪፖርት እንደሚደረግ መዘርዘር

የስልጠናው አጠቃላይ ቆይታ፡ 1 ሰዓት

የምስክር ወረቀትን በተመለከተ፡ በመጨረሻው ምዘና ቢያንስ 80% ላስመዘገቡ ተሳታፊዎች የውጤታማነት ሰርተፍኬት ይኖራል። የስኬት መዝገብን የተቀበሉ ተሳታፊዎች በተጨማሪም የኮርሱን Open Badge ማውረድ ይችላሉ። የበለጠ ለመረዳት እዚህ ላይ ይጫኑ።

የተተረጎመዉ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ቋንቋ *Podoconiosis: Training of health workers at national and district levels on skin-NTDs*, 2021 የአለም የጤና ድርጅት ለዚህ የትርጉም ስራ ይዘት ወይም ትክክለኛነት ኃላፊነት አይወስድም። በእንግሊዝኛዉ እና በአማረኛዉ ትርጉም መካከል ልዩነት ከተፈጠረ የመጀመሪያው የእንግሊዝኛ ስሪት አስገዳጅ እና ትክክለኛ ስሪት ይሆናል። ይህ የትርጉም ስራ በአለም የጤና ደርጅት አልተረጋገጠም። ይህ ግባዓት ለትምህርት ድጋፍ ዓላማዎች ብቻ የታሰበ ነው

Course contents

  • መግቢያ :

    ይህ የመግቢያ ሞጁል ትኩረትን የሚሹ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች (NTDs) ፣ የቆዳ ላይ-NTDs እና የፖዶኮኒኦሲስ በሽታን አጠቃላይ ምልከታ ይሰጣል
  • ሞጁል 1: የበሽታው ስርጭት፣ ስነ-አዕምሮአዊ፣ ማህበረሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች:

    በዚህ ሞጁል መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቅ፡የፖዶኮኒኦሲስ በሽታን ሊያመጡ የሚችሉ አጋላጭ ሁኔታዎችን ቀስቃሽ ምክንያቶችን ማብራራት፣ ስነ-ምድህራዊ የእድሜ እና የጾታ ስርጭቱን መግለጽ፣ ሊያስከተል የሚችለውን ስነ-አዕምሮአዊ፣ ማህበረሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች ማብራራት
  • ሞጁል 2፡ የበሽታው ልየታ እና ህክምና:

    በዚህ ሞጁል መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቅ፡ የበሽታውን አቀራረብና ስርጭት ፍንጮችን መግለጽ፣ ሊመሳሰሉ የሚችሉ ሌሎች በሽታዎችን መዘርዘር፣ ክሊኒካል የበሽታ ልየታ ላይ እንዴት እንደሚደረስ መግለጽ፣ የፍርንት የእግር ላይ እብጠት እንዴት እንደሚታከም ማብራራት፣ ታካሚዎች እንዴት መመከር እንዳለባቸው ማወቅ
  • ሞጁል 3: ተጨባጭ ለውጦች፣ የህብረተሰብ ጤና ስራዎች ትግበራ:

    በዚህ ሞጁል መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቅ፡: የህብረተሰብ ጤና ጣልቃ -ገብነቶችን መግለጽ፣ በሽታውን በመቆጣጠር የተገኙ ተጨባጭ ለውጦችን እንዴት እንደሚለካ መግለጽ
  • ሞጁል 4: መረጃ ማጠናቀር እና ሪፖርት:

    በዚህ ሞጁል መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የሚጠበቅ፡ የበሽታዉን ፍቺ ማብራራት, እና ፖዶኮኒዮሲስን ለማጥፋት የሚደረገውን ሂደት ለመከታተል እና ለመገምገም የሚረዱ ዋና ዋና አመልካቾችን መዘርዘር

Enroll me for this course

The course is free. Just register for an account on OpenWHO and take the course!
Enroll me now

Certificate Requirements

  • Gain a Record of Achievement by earning at least 80% of the maximum number of points from all graded assignments.
  • Gain an Open Badge by completing the course.